“በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በኤጀንሲው ተከብሯል፡፡

የዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው በንግግራቸው እንደገለጹት የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የሚከበረው አዲስ ፓርላማ እና የመንግስት ምስረታ በተካሄደበት ማግስት እና በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለመገንባትና ብልፅግናን ለማምጣት አዲስ ምእራፍ በጀመርንበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል በማለት እኛም እንደ ዜጋ በአዲስ ራዕይ እና በአዲስ ተስፋ ሃገራችንን ማገልገል አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ ሀገር ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚያንፀባርቁበት የሀገራዊ አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው፡፡
በፕሮግራሙ የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ ታድመዋ፡፡

የሲ.ማ.ድ.ኤ. የኮሚዩኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት