የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ህብረቶች ጋር በመሆን በአዳማ ከተማ ኦቦ ፓርክ ከአምስት ሺህ በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በምትገኝበትና ከየአቅጣጫው የተጋረጠባትን ጫና ለመመከት በምታደርገው ጥረት ጀግናውን የአገር መከላከያ ሰራዊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሎጂስቲክስና በገንዘብ መደገፍ ይጠበቅበታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ድርጅት ከዓላማው ውጪ ሲንቀሳቀስና ለጠላት ወግነው ሲሰሩ የተገኙ ድርጅቶች ላይ እርምጃዎች ተጠናክረው የሚቀጥል መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን ለህብረተሰብ የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገር እድገትና ብልጽግና የሚሰሩ ድርጅቶችን እያገዝንና እየደገፍን የምንቀጥል መሆኑን እገልፃለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

በመጨረሻም ለ3ኛ ጊዜ በምናከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራችን በድል ተሻግራ በብልጽግና አረንጓዴ ሆና ለትውልድ እንደምትቀጥል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሙሐመድ በበኩላቸው በእንደዚህ አይነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ለሀገርና ለህብረተሰቡ ጥቅም የሚሰጡ እስከሆኑ ድረስ በግላችን ሀላፊነቱን ወስደን እንዲሁም ከኤጀንሲው ጋር በመሆን እንቅቃሴዎችን ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ይህንንም አጠናክረን በመቀጠል በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ለሀገር ልማትና ለህብረተሰብ የላቀ ተጠቃሚነት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

 

ሀገር በአንድ ወገን ጥረት ብቻ አትበለፅግም ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ እኛም ተነሳሽነቱን ወስደን ከ1500 በላይ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን ያቀረብን ሲሆን ይህም ከሀሳብ በዘለለ የድርሻችንን በተግባር እየተወጣን እንደሆነ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ሀገር በአንድ ወገን ጥረት ብቻ አትበለፅግም ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ እኛም ተነሳሽነቱን ወስደን ከ1500 በላይ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን ያቀረብን ሲሆን ይህም ከሀሳብ በዘለለ የድርሻችንን በተግባር እየተወጣን እንደሆነ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ከ400 በላይ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ አጠቃላይ ሰራተኞች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ህብረቶች ተሳታ ሆነዋል፡፡