በሃዋሳ የሚገኘው የሜሪ ጆይ የልማት ማህበር ተጎበኘ፡፡

የኤጀንሲው ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ቡድን መሪዎችና ከባለሙያዎች የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ድጅቱን ጎብኝቷል፡፡

ሜሪ ጆይ ከተመሰረተ 20 ዓመታትን ያስቆጠረ በተጠቃሚዎች ህይወት ላይ የዘለቄታ መሻሻልን የሚያመጣ ቀጣይነት ያለው ድርጅት መሆን የሚል ራዕይ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በማዕከሉ ለአረጋዊያን እና ለህጻናት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ድርጅቱ በ118 ወረዳዎች ላይ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በማዕከሉ ለአረጋዊያ የማሳጅ፣የምግብ፣የጤናና የሞያ ስልጠና እና አገልሎት ይሰጣል እንዲሁም ለህጻናት የሙዚቃ ክህሎት ማዳበሪያ ትምህርት፣ሰርከስ እና የላይብረሪ አገልሎት የሚሰጥ መሆኑን ተመልክተናል፡፡

የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢዳር ዘውዴ ለጎብኚዎች ገለጻ ባደረጉበት ወቅት እንዳብራሩት ድርጅቱ ከተመሰረተበት ግዜ አንስቶ በጤና፣በሳኒቴሽን እና በትምህር ላይ በርካታ ስራዎችን የሰራ መሆኑን ገልጸው  ኢትዬጵያን መቀየር የምንችለው እኛ ልጆቿ ነን ብለዋል፡፡

ሲስተር ዘቢዳር አክለውም የሃዋሳው አረጋዊያን ማቆያ ኢትዬጵያውያን ለኢትዬጵያውያን በሚል በመንግስት፣በግል ባለሃብቱ እና በማህበረሰብ  ጥረት በውስጥ ሃብት  ገቢ በማሰባሰብ የተሰራ ማዕከል መሆኑን አብራርተው ሃብትን ፍለጋ ወደ ውጭ ከማማተር ይልቅ አጠገባችን ያለውን ግብዓት በአግባቡ በማየት መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

.

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ከጉብኝቱ በኋላ እንደገለጹት ይህንን የመሰለ ስራ እንድንመለከት እድል ስለሰጣችሁን ከልብ እናመሰግናለን በማለት አንድ ሰው ስንት ሰው ነው? በማለት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ይህን ያልኩት ይላሉ ዋና ዳይሬክተሩ የዚህ አይነት የከበረ ስራ የሚሰራ ከፊትም ከኋላም አሻግሮ የሚመለከት እና ለሃገር ትልቅ ስራ የሚሰራ ሰው ከአንድ በላይ ነው አንቺ የዛ ምሳሌ ነሽ በማለት ሲስተር ዘቢዳርን አሞግሰዋል፡፡

በጎ ፍቃደኞች ሃብት፣ገንዘብ ወይም ጤናም ባይኖራቸው ልብ ስላላቸው ብዙ ስራዎችን ይሰራሉ ዛሬ በዚህ ድርጅት የተመለከትነው እሱን ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በባዛርና ኤግዚቪሽን ዓላማ ብለን ያስቀመጥነው የመንግስት፣የግሉዘርፍ እና የማበረሰቡን የተቀናጀ ፕሮጀክት በዚህ ቦታ መመልከት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ በማለት በሜሪ ጆይ ማዕከል የተመለከትነው የአርቲስቶች የግል ባለሃብቱ እና የመንግስት ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ኤጀንሲው በሚችለው ሁሉ ድርጅቱን ለመደገፍ ጥረት ያደርጋል በማለት  የግሉ ዘርፍ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ድርጅቶችም ወደ ውጭ ከመመልከት ይልቅ የውስጥ አቅምን መጠቀም ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በአረጋዊያኑ  ማዕክል ችግኝ በመትከል ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡