ዋና ዳይሬክተር  ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በሃገራችን በርካታ ፈተናና ድሎችን ያስመዘገብንበት ዓመት መሆኑን ገልጸው በተለይ በሰሜን የሃገራችን ክፍል የተፈጠረው ችግር፣የኮቪድ ወረርሽኝ እና ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ከውጭ የነበረው ጫና ከነበሩ ፈተናዎች መካከል የሚጠቀስ መሆኑን አብራርተው 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ እና የሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በሰላም መጠናቀቁ ለሃገራችን ድል ነው ብለዋል፡፡

ከኤጀንሲያችን አንጻርም በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን ገልጸው እነዚህም 689 አዳዲስ ድርጅቶች መመዝገቡ፣የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ቀን መከበሩ፣የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ካውንስል መመስረቱ፣የክልል እና ከፌደራል ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር የጋራ ጉባኤ መመስረቱ እና ቦርዱም  ስራ መጀመሩ ከነበሩ ጥሩ አፈጻጸሞች ውስጥ የሚጠቀሱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በኤጀንሲው የተመዘገቡ ውጤቶች በሙሉ ሰራተኞች በራስ ተነሳሽነት እና ጥረት ስራዎችን መስራታቸው እንዲሁም በሰራተኞችና በአመራሮች ቅንጅታዊ አሰራር የመጣ ውጤት ነው ብለዋል ፡፡

የዛሬው መድረክ ዋና ዓላማም በዓመቱ ያከናወናቸውን ስራዎችና ድሎችን በማክበር የበለጠ ለመስራትና ክፍተቶችም ካሉ አሻሽሎ ለበለጠ ስራ ለመዘጋጀት ነው ያሉ ሲሆን  በሃገራችን ከተመረጡ አራት ዘርፎች መካከል የኛ ዘርፉ አንዱ በመሆኑ ከዚህ የበለጠ አጠናክሮ በመስራት ለሃገር እድትና ልማት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

በመጨረሻም በተቋሙ የተመዘገቡ ውጤቶች በሰራተኞች ጥረት በመሆኑ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡