የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ሁሉ ለሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግጭት አባባሽ የሆኑ ጉዳዬችን የሚቀርፍ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ፡፡
ይህ የተባለው “የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በሐዋሳ ከተማ በተደረገ የአንድ ቀን የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት መንግስት በሀገር ግንባታ ተዋንያን መካከል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መሆናቸውን በመረዳት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው ይህ

ምናልባት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ምስል የውይይት መድረክም የዚሁ አካል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በዲሞክራሲ፣በሰላም ግንባታ፣በህዝብና በመንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ድርጅቶች በስራዎቻቸው ሁሉ ለሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግጭት አባባሽ የሆኑ ጉዳዬችን የሚቀርፍ መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውክልናቸው የህዝብ በመሆኑ ማኅበረሰብን የሚጠቅም ተግባር እንጂ ፈንድ የሚሰጥን አካል ዓላማ ለማስፈጸም መሆን አይገባውም ሲሉም አሳስበዋል፡፡
የአፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው እንደ ሀገር ያለምነውን ብልጽግና ለማምጣት ሰላምን ማጽናት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ከዚህ ረገድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡ ይህንኑ ተፈጻሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ (MOU) ተፈራርሞ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሰላምን ለማስጠበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እና የንቅናቄ መድረኮችን መፍጠር፣ ለሠላም ግንባታ አጋዥ የሆኑ እስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን መለየትና ለመንግስት የፖሊሲ ግብዓት እንዲሆን ማቅረብ፤ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመድረኩ ዶ/ር አወቀ አጥናፉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ እና አቶ ገመቺስ ኢቲቻ የሰላም ሚኒስቴር የሀገር ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ውይይቱን መርተዋል፡፡