
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዴስክ ኃላፊዎች የጋራ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ተካሄደ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በየ6 ወሩ የሚያካሂደው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ አስተባባሪዎች እንዲሁም በክልልሎች የሚገኙ የፍትህ ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምዝገባ ተወካዮች የሚሳተፉበት የጋራ መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የጋራ መድረኩን በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማሞ ሞሊሶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መድረኩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌደራልና ከክልል የባለድርሻ አካላት ጋር ከሚያደርገው የጋራ ጉባዔ አስቀድሞ የሚካሄድ ሲሆን ክልሎች ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ያከናወኗቸውን ተግባራት በሚመለከት ሪፖርት የሚያቀርቡበትና በአጋጠሙ ችግሮች ላይ በመወያየት የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥ የሚያግዝ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክልሎች ጋር በቅርበት በመስራት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወኗቸውን ተግባራት በመቀመር ዘርፉ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እየሰራ ይገኛል።


