
ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የበጎ ፈቃደኝነት ባህልና እሴትን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስጠናዎች መሰጠት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በጎ ፈቃድ አብሮነትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጎለብት፣ማኅበራዊ መስተጋብር እንዲጠናከር፣ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር፣ የልማት ዓላማ ግቡን እንዲመታ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለሀገር ካለው ጥቅም አንፃር ባህል እንዲሆን፣ በጎ ፈቃደኞች ለሀገር እና ለወገን ያላቸውን ፍቅር በተግባር እንዲገልጹ ለማስቻል ዋንኛ መሳሪያ ነው፡፡
ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ 1113/2011 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህልና እንቅስቃሴ ማበረታታት፣ የበጎ ፈቃደኝነትን በተመለከተ የስርጸት ስራ መስራት አንዱ ሲሆን የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እና በጎ ፈቃደኝነት በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ለማድረግ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የተሰጠውን ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከCrossroads international ጋር በመተባበር በጅማ ዩኒቨርስቲ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ በበጎ ፈቃድ ላይ ለሚሳተፉ ተማሪዎች እና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በበጎ ፈቃደኝነትና በጎ አድራጊነት ባህል ዙሪያ እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ክበባትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙልነህ እንዲሁም የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እንዲሁም የተማሪዎች አገልግሎት ሀላፊ ዶ/ር ተስፋዬ አጋ እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እንደተናገሩት በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ተማሪዎች መሳተፍቸው ጠቀሜታዎች እንዳሉት በማውሳት በዋናነት ዜጎችን ለማነፅ፣ ለህብረተሰብ በጋራ ለመተሳሰብ ፣ለህብረብሄራዊ አንድነት ጭምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የጅማ ዩኒቨርስቲ በማህበረሰብ አቀፍ የትምህርት ፍልስፍና እንደሚታወቀው ሁሉ ተማሪዎች በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ በመሳተፍ ከማህበረሰቡ ጋር በመስራት ከራሳቸውን እውቀት ጋር በማስተሳሰር ችግሮችን በመፍታት ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
ተማሪዎች ያላቸውን እውቀትና አቅም በማስተባበር አቅመ ደካሞችንና ችግረኞችን ቀና ማድረግ ስራ ለመስራት በበጎ ፈቃደኝት ዙሪያ ስልጠናዎችን በመውሰድ አቅማቸውን መገንባት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡:
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በዚህ ወቅት ለጂማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ስልጠናዎችን ለመስጠትና ለዩኒቨርስቲው ጋር በጋራ ለመስራት ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በስጠናውደ ላይ የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅኝቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ዙሪያ እየሰጠ ያለው ስልጠና ተማሪዎች የበጎ ፈቃደኝነት ባህልና እሴትን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑን አንስተው ወጣቶችም በታማኝነት አገርን ማገልገል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
አክለውም ማንኛውም ዜጋ በጎ ፈቃደኝነትን እሴትና ስነ-ምግባር በመላበስ የዕለት ተዕለት ህይወታቸው አካል ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ ስልጠና የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ለCrossroads international እና ለጅማ ዩኒቨርርቲ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን፣ በበጎ ፈቃድ ዙሪያ እና (vmis) ፕላት ፎርም ላይ ለተማሪዎች ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡

