
ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን በእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት (MCMDO) የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ በእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት (MCMDO) የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱን ጨምሮ፣ከክልልሉ፣ ከዞንና ወረዳ የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ድርጅቱ በኮሬ ዞን አዲስ የቦኖ ግንባታ እና የውሃ መስመር ዝርጋታ ስራዎችን፣በጤና ጣቢያዎች ላይ መድሃኒት የማቅረብ እና የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ምርጥ ዘር ከማቅረብ ረገድ የሰራቸውን ስራዎች መመልከት ተችሏል፡፡
ሚስ ሚዶ (MCMDO) 1977 የተመሰረተ እና በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በጤና ፣በትምህርትና ውሃ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሃገረ በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሙሉጌታ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በኮሬ በዞኑ በተሰራው ስራ ከ43 ሺህ በላይ ማህበረሰብ ተጠቃሚ መሆኑን አንሰተው የዞኑ አስተዳደር ተባባሪነትና የህዝቡ ለልማቱ አጋዥ መሆን የታቀዱ የልማት ስራዎች በአጭር ግዜ ሊጠናቀቅ እንዳስቻለው ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት መንግስት ከለውጡ በኋላ በዘርፉ የህግና ተቋማዊ ሪፎርም ማድረግ መቻሉ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በእቅዳቸው መሰረት እንዲሰሩ እና ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል፡፡
በእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት (MCMDO) በኮሬ ዞን በአጭር ግዜ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው የማህበረሰቡ ጥያቄ ከዚህ በተሻለ ለመመለስ ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የአከባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየትም ድርጅቱ በዞኑ የማህበረሰቡን ችግር እየቀረፈ መሆኑን አንስተው ከህዝብ ቁጥር እና ፍላጎት አንጻር ፕሮጀክቱ እንዲቀጥልላቸው እና ሌሎች መሰል ድርጅቶችም ወደ ዞኑ መጥተው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Tagline
Long headline on two lines to turn your visitors into users
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.


Tagline
Long headline on two lines to turn your visitors into users
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.

