በባለስልጣን መስሪያቤቱ እያንዳንዱን ተግባር በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የጀመረው ስራ አበረታች መሆኑን በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተገለጸ፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላቱ በባለስልጣን መስሪያቤቱ በባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በአካል በመገኘት ተመልክተዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ አባላት የባለስልጣን መስሪያቤቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ከየስራ ክፍሉ የተውጣጡ ባለሙያዎችና አገልግሎት ፈልገው ወደ ተቋሙ የመጡ ደንበኞችን አነጋግረዋል፡፡ በምልከታቸውም ባለስልጣን መስሪያቱ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተጀመረው ተግባር አበረታች መሆኑን፣የክትትልና የድጋፍ ስራው ፣መንግስትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በቅንጅት ተግባራትን በማከናወን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወነ ያለው ተግባር፣የበጎ ፍቃድና የበጎ አድራጊነት ባህል በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲሰርጽ ግንዛቤ መፈጠሩ ፣ ከሚመለከታቸው የክልል፣የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓቶች እና ሌሎች በዘርፉ የተጀመሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በእቅዳቸው መሰረት እንዲያከናውኑ እና የላቀ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት በመስጠት ማከናወን እንደሚገባው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓቱ እንዲጠናከር የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትን ማጠናከር ይጠይቃል ብለዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተቋሙን ለመደገፍና በአካል ስለተገኙ ምስጋናቸውን አቅርበው ቋሚ ኮሚቴው የሰጧቸውን አስተያየቶች በማጠናከር ለተሻለ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት ተቋማቸው እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡