የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2017 የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸው ተገመገመ::
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ በተገኙበት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት እና የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የ2017 የስድስት ወራት እቅድ አፋጻጸማቸው ቀርቦ ተገምግሟል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ በማብራሪያቸው አንደገለጹት ሁሉም ተቋማት ከእቅድ አንጻር ያከናወኗቸው ተግባራት አበረታች መሆኑን አንስተው ተቋማት እቅዶቻቸውን ስትራቴጂክ መሆናቸውን ማረጋገጥና በዛ መሰረት መፈጸም ፣ሪፎርሙን የተረዳና የተገነዘበ ሰራተኛን ከመፍጠር አንጻር ትኩረት አድርጎ መስራት እና ዲጂታል ተቋም ከመገንባት አንጻር በተጠሪ ተቋማቱ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
አያይዘውም በፍትህ ሚኒስቴር መታየት የሚገባቸው ጉዳዬች ተለይቶ እንደሚሰራ ተናግረው ተጠሪ ተቋማት እቅድን መሰረት አድርገው ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሚኒስትር መስሪያቤታቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


