በ4ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች የተዳሰሱበት በርካታ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
ዛሬ በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለት ፓናል ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን ከዚህ መካከል ‹‹የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ›› የሚል ይገኝበታል፡፡
የፓናል ውይይት መነሻ ጹሑፍ ያቀረቡት አቶ መለሰ አለሙ በሚንስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባት ማስተባባሪያ የዘርፍ ሃላፊ እና አቶ አህመድ ሁሴን የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ም/ፕረዝዳንት ናቸው፡፡
በመነሻ ጽሑፉ መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ያደረጋቸው ሪፎርሞች፣የሚከተላቸው አቅጣጫዎች፣በዘርፉ ያሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ረገድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ምን መሆን እንደሚገባው ተገልጻል፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ በዲሞክራሲና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን በማንሳት በቀጣይ ማህበረሰብን ማዕከል ያደረገ ስራ መስራት በሚገቡ ጉዳዬች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው በማህበረሰቡ ዘንድ የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር ለማድረግ የውይይት እና የምክክር ባህል መጎልበት አለበት ብለዋል፡፡



