የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከጀስቲሰ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ኢትዬጵያ ጋር በመተባበር የሴቶችና ህጻናት መብት ጥበቃ እና ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ላይ ያተኮረ ስልጠና ከተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ ባለሙያዎች ሰጠ፡፡
May be an image of 11 people, table and dais
በስልጠናው ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጀስቲስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት አማካሪ ዶ/ር ዘሪሁን ይመር እንዳሉት ድርጅታቸው ለበርካታ ዓመታት በሴቶችና ህጻናት በሰላም ግንባታ በእርቅ ላይ እና በሰብዓዊ መብት የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለፅ በቀጣይም እቅዶችን በማዘጋጀት ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡ በክብር እንግድነት የተገኙት የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ እንዳሉት በሴቶች እና ህጻናት ላይ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ረዥም ዓመታት የነበሩ ስር የሰደዱ በአገራችንም ሆነ በአለም አቀፍ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ የመጣ አሳሳቢ ችግር መሆኑን በማንሳት ይህን ችግር ለመቅረፍ ለህብረተሰቡ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡
ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከልም ሆነ የመፍትሄ አካል ለመሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት እንዳለበት ም/ፕሬዝዳንቷ አሳስበዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የፕሮጀክት አስተዳደር አጋርነት ቡድን መሪ አቶ እድሪስ የሱፍ እንደተናገሩት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ሁሉም ዜጋ ሀላፊነት እንዳለበት በመጠቆም በተለይ በሴቶችና ህጻናት ላይ መሰረት አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች ከወትሮ በበለጠ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲጠናከሩ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ በመጥቀስ ይህ ስልጠና እንዲዘጋጅ ድጋፍ ያደረገው ጀስቲስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ኢትዮጵያ በማመስገን በቀጣይ በጋራ ለመስራት መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡