
ስልጠናው ተቋማዊ ለውጥ፣ውጤታማ ተግባቦት እና የስጋት አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት በባለፉት የሪፎርም አመታት ተቋማችን ቴክኖሎጂን የሚጠቀም እና የአሰራር ስርዓት የዘረጋ ተቋም ወደ መሆን ተሸጋግሯል በማለት ለውጥ የማያቋርጥ በመሆኑ እስካሁን ያስመዘገብናቸው ውጤቶችን በመያዝ ወደ ሌላ የተሻለ አፈጻጸም ሊያሳድግ ወደሚችል፣ በስነ-ምግባር የታነጸ ተቋም ለመገንባት እንሰራለን ብለዋል ፡፡ አያይዘውም በተቋሙ ዳግም ሪፎርም ከተጀመረ ሁለት ዓመት የሞላው መሆኑን በማንሳት በዚህ ሂደት የውስጥ አሰራርን ዘመናዊ ማድረግ እና የውስጥ እርካታን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለውጡን ለማሳካት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከነዚህም መካከል የAFD ፕሮጀክት በስልጠናና በውስጥ የዳሰሳ ጥናት ላይ ትኩረት አድርጎ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ለሰራተኞች ተከታታይ ስልጠና መስጠት እና ወደ ውጤት መቀየር ሲቻል የተሻለ ተቋምና ሀገር መገንባት እንችላለን አጠቃላይ ውጤቱም ጠንካራ እና የበለጸገች ሀገር የመገንባት ሚና ያለው ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡ ስልጠናው በአራት ዙር ለሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

