ተግባርና ኃላፊነት

 • የኤጀንሲዉን ተልእኮ ለማሳካት በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር አካላት እና የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶችን መለየት፣ በጋራ የሚሰሩ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችል የጋራ እቅድ እንዲዘጋጅ ማድረግ፣ አፈጻጸሙን መከታተል፤
 • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በእቅድ የተያዙ ተግባራት ለመገምገም የሚያስችል የግምገማ መድረክ ማዘጋጀት፣ አፈጻጸሙም እንዲገመገም ማድረግ፤
 • በቅንጅታዊ አሰራር ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን መለየት፣ ክፍተቱን ለመፍታት የሚያስችል የመፍትሄ አቅጣጫ ማመላከት፤
 • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ የሚሰሩ ተግባራትን የአፈጻጸም ደረጃ በአካል ተገኝቶ መገምገም፣ የታዩ ክፍተቶችን ለይቶ ማቅረብ፣
 • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ቀጣይነት ያለው የአሰራር ስርአት እንዲዘረጋ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ተቀናጅቶ መስራት፤
 • በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለ ድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች በተለዩ ክፍተቶች ዙሪያ ተቀባይነት ያገኙት የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፤
 • የኤጀንሲዉን ተልእኮ ለማሳካት የሚያስችል ሃብት ማፈላለግና ጥቅም ላይ እንዲዉል ማድረግ፤
 • ከአጋር አካላት በተገኙ ሃብቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገም፣ ግብረ-መል ስመስጠት፤
 • የማክሮ ኢኮኖሚና ፊዚካል ማዕቀፎችን መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ከዘርፉ ጋር እንዲተሳሰሩ ማድረግ፤
 • በሌሎች ሀገራት ያሉ መልካም አሰራሮች እና ልምዶች በማሰባሰብ ለሀገራችንና ለተቋሙ ተልዕኮ በሚስማማ መልኩ መቀመር፤ እንዲቀመር ማድረግ፣ ማረጋገጥ፣ በጥቅም ላይ እንዲውል መከታተል፣
 • ኤጀንሲው ከአለም አቀፍ ድርጅቶቸና አገር አቀፍ ድርጅቶችን መልካም የስራ ግንኙነት እና አጋርነት እንዲኖር ሁኔታዎች ማመቻቸት እና
 • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በተመለከተ ዘርፉ ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ከመሆኑ አንፃር እንደ ሀገር ያለው ባለሙያ ውስን ስለሆነ ከአለም አቀፍ ድርጅቶችና ከዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ሀገሮች ትምህርት፣ ስልጠና እና ልምድ የሚወሰድበትን መንገድ መዘርጋት፣ ማመቻቸት፡፡