የህግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ

  • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በተመለከተ የህግ ጥሰቶች ሲኖሩ ለክስ የሚያበቁ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ክስ ማዘጋጀት፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፋይል ማስከፈት፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መጥሪያ መቀበል፣ መልስ ማዘጋጀትና ኤጀንሲውን በመወከል በማናቸውም ጉዳዮች በህግ ፊት ቀርቦ መከራከር፤
  • የቃለ መሀላ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን  በሚመለከት የጣልቃ ገብ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤
  • የዕግድ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የመቃወሚያ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሚመለከት ጣልቃ ገብቶ መከራከር፣ ይግባኝ ክስ እና አቤቱታ ማቅረብ፤
  • የህግ ምክር አገልግሎት መስጠት፣ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር መመሪያዎች ማዘጋጀት፣ ፀድቀው ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ መመሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፤
  • በአዋጁ ላይ የሚታዩ የህግ ክፍተቶችን በየጊዜው መፈተሽና የህግ አስተያየቶችን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣ የህግ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
  • ለባለስልጣኑ የስራ ክፍሎች በህግ ነክ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንዲሰጥ መከታተል መስጠት፣ ማብራሪያ ወይም የህግ አስተያየት በፅሁፍ ማዘጋጀት፤
  • ከባለስልጣኑ  አዋጅ ጋር የሚዛመዱ አዋጆችን የማሰባሰብ፣ የህግ ግንዛቤ የሚሰጡ ፓምፕሌቶችን ማዘጋጀት እና ማሰራጨት እና
  • ከባለስልጣኑ ሠራተኞች ጋር በተገናኘ የሚነሱ የህግ ነክ ጉዳዮች ክርክር ባለስልጣኑ በመወከል በማንኛውም ደረጃ በሚገኙ ፍ/ቤቶች ቀርቦ መከራከር፡፡