የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከKVO INTERNATIONAL ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
በጎ ፈቃድ አብሮነትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጎለብት፣ ማኅበራዊ መስተጋብር እንዲጠናከር፣ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር፣ የልማት ዓላማ ግቡን እንዲመታ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለሀገር ካለው ጥቅም አንፃር ባህል እንዲሆን፣ በጎ ፈቃደኞች ለሀገር እና ለወገን ያላቸውን ፍቅር በተግባር እንዲገልጹ ለማስቻል ዋንኛ መሳሪያ ነው፡፡
ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ 1113/2011 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህልና እንቅስቃሴ ማበረታታት፣ የበጎ ፈቃደኝነትን በተመለከተ የስርጸት ስራ መስራት አንዱ ሲሆን የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እና በጎ ፈቃደኝነት በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ይህንንም ተግባር ወደፊት ለማስቀጥል ባለስልጣኑ KOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ ወቅት የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ ፣ አቶ መስፍን ሙልነህ እና ከKOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሚኪስ ግርም ተገኝተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት በመጀመሪያ በጎ ፈቃደኝነት ለማስተዋወቅ ከባለስልጣኑ ጋር አብሮ በጋራ ለመስራት ዝግጁ በመሆናቸው ምስጋናቸውን በማቅረብ በኢትየጵያ የበጎ ፈቃደኝነት ጉዳይ በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ሆኖ እንዲጎለብት ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እንዲሆን ስራዎችን ለመስራት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡
ሌላው ያነሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት ከተለያዩ አካላት ጋር በመነጋገር በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር በጎ ፈቃደኝነት የሚመራበት ፖሊሲ፣ መመሪያዎች እና ማንዋሎች የማዘጋጀት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አለም አሁን ከደረሰችበት ስልጣኔ አንጻር ወጣቱ እንዲሁም በውጭ የሚገኘው ዲያስፖራው በቴክኖሎጂ በማገዝ በጎ ፈቃደኝነትን በኦን ላይን ለማድረግና ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረቶች በማድረግ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን(vmis) ፕላት ፎርም በማዘጋጀት ተግባራዊ መደረጉን ገልፀው የዛሬ ፕሮጀክትም ዋና አላማ KOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ድርጅትም ከበጎ ፈቃደኝነት ጋርም በተያያዘ ልምድ ያለው በመሆኑ እና የበጎ ፈቃደኝነት ስራን ቀለል ለማድረግ የሞባይል አፕልኬሽን በመጠቀም አቅምና እውቀት ባለው መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ለወጣቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጎ ፈቃደኝነት በኢትዮጵያ ውሰጥ ስርዓት ተገንብቶለት የለት እለት ልምምድ እስኪሆን ድረስ አስፈላጊውን ስራ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን የቀረውን ጊዜ የሚያካክስ ስራዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ከKOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሚኪያስ ግርማ እንዳሉት የዛሬው የስምምነት ሰነድ እንድንፈራረም በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የባለስልጣኑ አመራሮች ከፍተኛ ድጋፍ ስላደረጉ ምስጋናቸውን በማቅረብ ድርጅታቸው በኢትየጵያ ከተቋቋመ ረጅም አመት ማስቆጠሩን ገልፀዋል፡፡
ካንትሪ ዳይሬክተሩ አያይዘውም በጎ ፈቃደኝነት ላይ ስራዎችን ለመስራት ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ አንደኛው ሪሶርስ ሲሆን ሁለተኛው የአመለካከት ለውጥ ነው ሲሉ የፕሮጀክቱም አካል ዋንኛው በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት በአመለካከት ላይ መሰራት ነው ብለዋል፡፡


