19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የፍትህ ሚንስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በተለያየ ዝግጅት አክብረዋል፡፡

19ኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በፍትህ ሚንስቴር አዳራሽ የፍትህ ሚንስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡ በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በፍትህ ሚንስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚንስትር ደዔታ አቶ ተስፋዬ ዳባ ሁለንተናዊ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ፍላጎት ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር አንድነታችንን በማይነቃነቅ አለት ላይ መገንባት እንደሚገባ ጠቁመው ለአሁናዊ ሀገራዊ ችገሮች የመፍትሄ አካል ከመሆን ባለፈ መጻዒ እድሎችን ማመቻቸት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በኢተዮጵያ ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ በፍትህ ሚንስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚንስትር ደዔታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ያቀረቡ ሲሆን ሰነዱን መነሻ በማድረግ ውይይት ተደርጓል፡፡ በበዓሉ ላይ የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች በለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡