በጎ ፍቃደኛ የተቋሙ ሰራተኞች በጌርጌሴኖን በጎ አድራጎት ድርጅት በእውቀት እና በጉልበት የተለያዩ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያቤቱ የበጎ ፍቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊየን እንዳሉት በአዋጅ 1113/2011 ለተቋሙ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት በኅብረተሰብ ዘንድ የበጎ አድራጎትና በጎ ፍቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ረገድ የተቋማችን ሰራተኞች ሞዴል የበጎ ፍቃደኛ በማድረግ ለሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተምሳሌት ለመሆን እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ይህንን በጎ ተግባር በመቀላቀል በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሹ አካላትን በተለያየ መልኩ ማገዝ ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አቶ መለሰ አየለ የጌርጌሴኖን በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞች ላከናወኑት ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበው በበጎ ፍቃደኞች ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ የአይምሮ ህሙማኑ የሚጠይቃቸው፣የሚጎበኛቸውና የሚያናግራቸው ሰው ይሻሉ ብለዋል፡፡




