የባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

የሲሺል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ገለጻ ያደረጉት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ እንደገለጹት FSS ከ25 አመታት በፊት በአንጋፋ ምሁራን የተመሰረተና በማህበራዊና ልማታዊ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ጥናትና ምርምር የሚያካሂድ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት እንዲያደርጉ መድረኮችን የሚያዘጋጅና በመንግሥት የፖሊሲ አወጣጥና ትግበራ ሂደት የበኩሉን ድርሻ የማበርከት ዓላማ አንግቦ የተመ
ሰረተ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ለሙያ ማህበራት በተለይም ጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት አድርገው ለሚሰሩ ድርጅቶች (Think thanks) ድጋፍና አገልግሎት የሚሰጥ የተለየ የስራ ክፍል ያቋቋመ መሆኑን ገልጸው የተጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ጠቁመዋል።


