የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬከተር አቶ ፋሲካው ሞላ የአምስተኛውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ በቢሮአቸው አግኝተው አነጋግረዋል፡፡
ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ከነበረው በላቀ ሁኔታ እንዲከበር እና በሂደቱ መከናወን ስለሚገባቸው ጉዳዬች አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
የኢፌዲሪ ሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሮግራሙን በጋራ የሚያዘጋጁት ሲሆን አምስተኛውን አመታዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ለመሳተፍ ምዝገባ ተጀምሯል፡፡
በዝግጅቱ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያከናወኗቸውን ተግባራት በኤግዝቢሽን አማካኝነት ለህዝብ ይፋ ከማድረግ አልፎ፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ፣ የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላቶችን በተለያዩ የውይይት መድረኮች ይሳተፋሉ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዋነኛ አላማ በዘርፉ ያሉ ድርጅቶች በማህበረሰቡ ውስጥ በሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለህዝብ እና ለባለድርሻ አካላት እንዲያስተዋውቁ ዕድሉን መፍጠር እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከመንግስት፣ ከግሉ ዘርፍ እና ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር ተቀራርበው በትስስር የሚሰሩበትን መድረክ ማመቻቸት ነው።
ለመመዝገብ: https://forms.gle/9X9dRH8FkRMj5hAF9


