20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተከበረ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ሁነቶች አክብረዋል።
በበዓሉ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን “ዴሞክራሲ እና የፌዴራል ሥርዐት በኢትዮጵያ፣ ተስፋዎቹ እና ተግዳሮቶቹ” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።


በዓሉን በሚመለከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ አገራዊ በሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ አገራዊ መግባባትን መፍጠርና የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ ሂደቱ የሚጠናከርበት ተግባር ማከናወን፣ ከምንም በላይ የተሰጠንን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የመምራት ሃላፊነትን በአግባቡ በመወጣትና እንደመንግስት ሰራተኛ ለህግና ደንቦች ተገዢ መሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
አክለውም ፌዴራላዊም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሚገነባው በጉዳዮቹ ዙሪያ ሳይንሳዊ እና ተቀራራቢ የሆነ አረዳድ ሲኖርና እና ለሥርዐቶቹ መገንባት ተፈላጊ የሆኑ አስተሳሰቦችን መላበስ ሲቻል መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ረገድ ሁሉም ሰራተኛ የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።


