የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከባለድርሻ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ለግማሽ ቀን የቆየ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተወካዮችና የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ውይይቱ የተደረገው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ቀደም ሲል በነበረው ውይይት ተሰጥተው የነበሩ ሃሳብና አስተያየቶችን በማከል ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የተደረገ የውይይት መድረክ ነው፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩ ሲሆን ረቂቅ ማሻሻያውን በሚመለከት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ለውይይቶቹ ምላሽና ማብራሪያ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዲሁም አቶ አዲስ ጌትነት በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ተሰጥቷል፡፡



