ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለአጋሮ አጠቃላይ ሆስፒታል ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በቦታው በመገኘት አበረከተ፡፡ በርክክቡ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ የጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በፍቃዱ ወልደሰንበት እንደተናገሩት ባለስልጣኑ በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የመመዝገብ የመደገፍ የመከታተል እና የመቆጣጠር ሀላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ተቋም መሆኑን በመግለፅ በዋናነት የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከተለያዩ ከተዘጉ ድርጅቶች ያገኛቸውን ንብረቶች ተመሳሳይ ዓላማ ላላቸው ድርጅቶች እንዲሁም ህብረተሰቡን ለሚያገለግሉ የመንግስት ተቋማት ንብረቶችን የማስተላለፍ ስራዎችን እንደሚሰራ በመግለፅ ለአጋሮ አጠቃላይ ሆስፒታል የተደረገው ድጋፍ እየሰጠ ካለው አገልግሎት አንጻር ያሉበትን የቁሳቁስ ችግሮች ለመቅረፍ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡


የአጋሮ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሪያድ እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሆስፒታሉን ችግሮች በመረዳት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በንብረት ርክክቡ ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ሻፊ እንዳሉት አጋሮ አጠቃላይ ሆስፒታል ያለውን ችግር በመቋቋም ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በማመስገን ህብረተሰቡ ከሆስፒታሉ አመራሮች ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሆስፒታሉ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም የተጀመሩ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ አጋርነቱን ማሳየት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡


