ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በአካታች አገራዊ ምክክር ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና በተመለከተ ተወያየ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ዝርዝር ውይይት አድርጓል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር አፈፃፀም በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የቀረበ ሲሆን በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በባለስልጣኑ አመራሮች በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
May be an image of 12 people and text
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ቋሚ ኮሚቴው ከዚህ ቀደም ለባለስልጣኑ የሰጠው የአፈጻጸም ግብረ መልስ በማኔጅመንት ደረጃ የተገመገመ መሆኑን በማውሳት ከተከበረው ቋሚ ኮሚቴ የሚሰጠው አስተያየትና አቅጣጫ አፈፃፀምን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በትኩረት እንደሚተገብሩ ገልፀዋል፡፡ በውይይቱ ባለስልጣኑ አዳጊ በሆነ መልኩ መልካም አፈፃፀሞችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቴ እና በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተጠቀሰ ሲሆን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተጨባጭ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲያከናውኑ የበለጠ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች መከናዎን ያለባቸው መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ተገልፆል፡፡ የአካታች አገራዊ ምክክርን በተመለከተ የውይይት ፅሁፍ በአቶ አህመድ ሁሴን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ቀርቦ በቋሚ ኮሚቴው አባላት ውይይት የተደረገበት ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአካታች አገራዊ ምክክሩ ውጤታማ መሆን እንዲችል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት አሳስበዋል፡፡