May be an image of 1 person and textበጉባኤው በርካታ ርዕሰ ጉዳዬች የተዳሰሱ ሲሆን በተለይም ጉባኤው ከተጀመረ ጀምሮ የተሻሻሉ እና የተገኙ ውጤቶች ፣የሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዴስክ ሃላፊዎች የተወያዩባቸው ርዕሰ ጉዳዬች ፣የራስ በራስ የማስተዳደርና ልምምድ እና አተገባበር በኢትዬጵያ ፣የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃና ኢነርጂ ላይ ከሚሰሩ የሲማድ ጋር የጀመራቸውን መልካም ስራዎችን በተመለከተ እና CSSP2 በዘርፉ እያከናወናቸው ስላሉ ጉዳዬች ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በማጠቃለያውም የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ጉባኤው ከግዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች እያሳየ መምጣቱን አንስተው ይህንን ጉባኤ ለማጠናከር ሁሉም ክልሎች እና ሴክተር መስሪያቤቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየዘርፍ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መደገፍ፣መከታተልና፣መቆጣጠር እንዲሁም በጉባኤ የተሰጡ አቅጣጫዎችን መፈጸም እና በቀጣይ መገምገም የዚህ ጉባኤ ቁልፍ አቅጣጫ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም ይህ ጉባኤ ተጀምሮ እዚህ እስኪደርስ ድረስ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ ላደረጉት CSSP2 ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡