በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያ የማነብርሃን እንደገለጹት ባለስልጣን መስሪያቤቱ ላለፉት ዓመታት ባካሄደው ውጤታማ ሪፎርም መልካም ስኬቶች ማስመዝገብ መቻሉን እና የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም ያለው ተቋም መገንባቱን አንስተዋል፡፡ ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተፈጠረው ምቹ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ ሁኔታ ሲማዶች በአገራዊ ጉዳዮች በስፋት ተንቀሳቅሰው ህዝብን የሚጠቅሙ ስራዎችን ማከናወናቸውን አንስተው ይህ የተጀመረው መልካም ስራ ከፍ ባለ ደረጃ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡    ሚኒ

May be an image of 5 peopleስትሩ አክለውም ሲማዶች የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ህግን አክብሮ በመንቀሳቀስ ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተው ወሳኝ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለ

ይም በሽግግር ፍትህ፣ በአገራዊ
ምክክር፣ በህግ የበላይነት፣ በዘላቂ ሰላም እና ግጭት አፈታት ዙሪያ በሚደረገው ጥረት ትርጉም ባለው መልኩ አዎንታዊ ሚና መጫዎት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደተናገሩት በባለፉት 6 ወራት ከክትትልና ድጋፍ አንጻር፣ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ እንዲሁም ሌሎች በአዋጁ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነት መሰረት ያደረገ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት ከተመዘገቡ ውጤቶች ባሻገር ውስንነቶች መኖራቸውን ገልጸው በቀጣይ 6 ወራት የማካካሻ ስራዎችን ጭምር በማከናወን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡የሲማድ ዘርፍ የበለጠ የአገርና ህዝብን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ ተቋማችን የጀመረውን የሪፎርም ስራ አጠናክሮ ይቀጥላ ያሉ ሲሆን የመድረኩም ዓላማ እቅድና ሪፖርቶችን በቋሚነት ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ለቀጣይ ስራዎች የሚጠቅሙ ግብዓቶችን ለማግኘት መሆኑን አስረድተዋል፡፡