የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በበጎ ፍቃደኝነት ስርፀትና አስተዳደር መምርያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ደርጅቶች ባለስልጣን በበጎ ፍቃደኝነት ስርፀትና አስተዳደር መምርያ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ለሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስርያቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የበጎ ፍቃደኝነትን በሀገራችን ባህል ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው የዚሁ አካል የሆነው የበጎ ፍቃደኝነት ስርፀትና አስተዳደር መመርያን በማዘጋጀት በየደረጃው ውይይት የማድረግና በቀጣይም በህትመት መልክ ለሚመለከታቸው አካላት ለማሰራጨት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በጎ ፍቃደኝነትን ማስረፅ እርስ በእርስ የመተባበር፣የመረዳዳትና የመተጋገዝ የመሳሰሉ የኢትዮጵያ መልካም እሴቶችን ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል ፡፡
አክለውም በጎ ፍቃደኝነት በሀገራችን ለማስረፅና ለማጎልበት የስራ ክፍል በማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም በበጎ ፍቃደኝነት ዙርያ እንደሀገር ንቅናቄ ለመፍጠር ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም የበጎ ፍቃደኝነት በሀገራችን ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር ተቋማቸው ይሰራል ብለዋል፡፡
መምርያውን ባማሳተም፣በማስተርጎምና የስልጠናውን ወጪ በመሸፈን ድጋፍ ላደረጉልን ዴቬሎፕመንት ኤክሰፐርቲዝ ሴንተር (Development Expertise Center) ምስጋና አቅርበዋል ፡፡