ተቋማችን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የጥራት ሽልማት ተሸላሚ መሆኑ የበለጠ መነሳሳትን ይፈጥራል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ባዘጋጀው 10ኛ ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ተቋማችን የከፍተኛ አድናቆት ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የጥራት ሽልማት ሂደቱ ዛሬ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር የጋራ የተደረገ ሲሆን በመድረኩ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት ይህ ሽልማት ትርጉሙ ብዙ ነው በተለይም ለበለጠ ስኬት አቅምና ተነሳሽነትን ለመስራት ብሎም ከዚህ የበለጠ ሰርተን ሞዴል የሆነ ተቋም ለመገንባት ስለሚያዝ ነው ብለዋል፡፡
በሁለተኛው የለውጥ ምዕራፍ ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ማሳካት አለበት ከወረቀት ነጻ የሆነ በዲጂታል የታገዘ ተቋም መገንባት፣በስራችን ስፔሻላይድ ማድረግ እና የውስጥ አሰራራችንን የበለጠ ማሻሻል የሚል ሲሆን ያገኘነው ሽልማት ይህንን ለማሳካት መነሻ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡
አቶ ሃይለስላሴ ገ/ሚካኤል ተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ ይህ ውድድር በርካታ መስፈርቶችን አልፎና ተገምግሞ የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸው በዚህ ሂደት የተጉ የተቋሙ ከፍተኛ ሃላፊዎች፣የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞችን አመስግነዋል፡፡
በዚሁ መድረክ ላይ ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት ሂደቱ በጣም አድካሚ እና በውጤት የተጠናቀቀ መሆን መደሰታቸውን በማንሳት ከሂደቱ ደካማ እና ጠንካራ ጎናችንን ለመለየትና በቀጣይ የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን እንድንሰራ መነሳሳት ይፈጥራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡