ለተቋሙ የማኔጅመንት አባላት በሃብት አሰባሰብ እና አስተዳድር ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በስልጠናው ላይ ባደረጉት ንግግር በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀፅ 86 መሰረት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የሚተዳደር የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ እንደሚቋቋም መደንገጉን በመግለፅ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በሃብት አሰባሰብና አስተዳድር ላይ ግንዛቤ በመያዝ ግልፅ አሰራር መዘርጋት ይጠበቅበታል ብለዋል።
.
አዋጅን መሰረት በማድረግ የወጣው የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ አስተዳደር መመርያ ቁጥር 848/2014 መሰረት በፈንዱ ተጠቃሚ የሚሆኑት በባለስልጣኑ ተመዝጋቢ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ የፈንዱም አላማ በጎ ፈቃደኝነት እና የዘርፉን እድገት ማበረታታት ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አገራዊ አስተዋጽዖ እና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዙርያ የሚሰሩ ድርጅቶችን ማበረታታትና ማገዝ ነው፡፡