የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የሥልጠናው ዓላማ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሚያደርገው ሀገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ ማጎልበት ንቅናቄ በበጎ ፈቃድ ማጎልበት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የበጎ ፈቃድ ማጎልበትትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን እንደተናገሩት ለማህበረሰቡ የበጎ ፈቃድን የሚያጎለብቱ ተከታታይ ስልጠናዎችንና ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎችን መፍጠር ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚጠበቅ በመሆኑ ይህንኑ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ሊዘጋጅ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡