የፌዴራል ፐፕሊክ ሰርቪስ መስሪያቤቶች የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ትግበራና የአፈጻጸም ምዘና መመሪያ ዙሪያ ለተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው እንዳሉት የዚህ ስልጠና ዓላማ የስራ ምዘና ስርዓታችንን ውጤታማና በጥራት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ እና በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ብሎም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው በርካታ ጉዳዬች ተነስተው ውይይትና ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡