የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሴት ሰራተኞች ፎረም በተሻሻለው የቤተስብ ህግ ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተሻሻለው የኢፌዲሪ የቤተሰብ ህግ ላይ ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች ስልጠና የሰጠ ሲሆን የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ፎረም የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸሙንና የ2016 በጀት ዓመት እቅድን በሚመለከት ውይይት ተደርጓል፡፡ በመድረኩ የተጓደሉ የፎረም አመራሮችን የሟሟላት እና ፎረሙን የማያጠናክር ስራ ተከናውኗል፡፡
በውይይቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴት ሰራተኞች ፎረም አባላቱን ለመደገፍ የተለያዩ ስልጠናዎችን ከአጋር አካላት ጋር በማዘጋጀት የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ውጤታማ ስራ መስራት እንዲችሉ ሲሰራ እንደቆየ የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም የፎረሙን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የበለጠ ውጤታማ ስራ ለመስራት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ሁሉም የተቋሙ ሴት ሰራተኞች በፎረሙ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተቋሙን ሴት ሰራተኞች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚሰራ የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ውጤታማ እና ለውጥ የሚያመጣ ፎረም እንደሚያስፈልግ ገልጸው ከተለያዩ ተቋማት ልምድ በመውሰድ እና በተለያየ ጊዜ የሚዘጋጁ መድረኮችን በመጠቀም መጠናከርና ወደፊት መምጣት ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የፎረሙን የተጓደሉ አመራሮች የተካ ሲሆን ወደተቋሙ በዝውውር የመጡ ሴት ሰራተኞች የፎረሙ አባል አድርጎ ተቀብሏል፡፡