የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለ11ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርኃ ግብር አከናውኗል፡፡

የደም ልገሳ መርኃ ግብሩ በዋነኛነት የተቋሙ ሰራተኞች በበጎ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ እና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል በተቋሙ ሰራተኞች እንዲዳብር ማድረግን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በቋሚነት በየሶስት ወሩ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በደም ልገሳ መርኃ ግብሩ ላይ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡