ለተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በፍቃዱ ወ/ሰንበት የሰራተኛውን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት፣ በብቃትና በእውቀት ስራዎችን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው በዘንድሮ በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ስልጠናዎች ለመስጠት በእቅድ መያዙን እና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ የአገልግሎት አሰጣጥ፣የበጎ ፍቃድ ምንነት፣የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ህዝባዊና ሃገራዊ ፋይዳ ፣በሃገራችን ያለው የበጎ ፍቃድ አተገባበር እና ሌሎች ጉዳዮች በሰነድ ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡