የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ Heavenly culture, World peace, Restoration of Light የተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ማናጀር ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ፡፡

Heavenly culture, World peace, Restoration of Light መቀመጫውን በኮሪያ ያደረገው ድርጅት በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ለመክፈት የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታዎች በተመለከተ ከባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጋር ፍሬያማ ውይይት አድረገዋል ፡፡
በውይይቱ ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት በሰላም፣በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ረገድ የሚያግዝና የሚያበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አያይዘውም Heavenly culture, World peace, Restoration of Light ድርጅትም በኢትዮጵያ ከሰላም አንጻር ለመስራት በማሰቡ ምስጋናቸውን በማቅረብ ባለስልጣኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡ የድርጅቱ ዳይሬክተር በበኩላቸው ድርጅታቸው ከ20 በሚበልጡ አገራት ላይ ሰላምን ከማስፈን አንጻር በርካታ ስራዎች እየሰሩ መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያም ቅርንጫፍ ቢሮ በመክፈት ያላቸውን ልምድና ተሞክሮዎችን ለማካፈል አንዳሰቡ ተናግረዋል፡፡