ሪች ኢትዮጵያ የተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቲቢ በሽታ መከላከል ላይ ላደረገላቸው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቀረቡ::

ሪች ኢትዮጵያ በባለስጣን መስሪያ ቤቱ የተቋቋመ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን ዋና ዓላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው በቲቢ የተጠቁ ሰዎችን የመንከባከብና የመደገፍ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
የድርጅቱ ስራ አስክያጅ አቶ ቅጣው ተ/ማርያም እንዳሉት በአገራችን የቲቢ በሽታ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጉ፤ የተጀመሩ ድጋፎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በማሰብ ለባለስጣን መስሪያ ቤቱ ምስጋና ለማቅረብ መምጣታውን ገልፀዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንዳሉት በአገራችን ተስፋፍቶ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የቲቢ በሽታ ከአገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲጠፋ እየተደረገ ባለው ስራዎች ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ በመግለፅ በቲቢ መከላከልና መቆጣጠር ላይ የሚሰሩ ድርጅቶችን ለመደገፍ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡