ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ CERFODES ከተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጋር ተፈራረመ፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እያከናውነ ያለውን ተቋማዊ ለውጡን ከግብ ለማድረስ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅሙን ለማሳደግ ከAFD ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ the establishment of a project management unit የተባለ ፕሮጀክት CERFODES ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር ዛሬ ተፈራርሟል፡፡
የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባላስልጣን አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በዘርፉ ላይ እዲሁም በተቋሙ የመጀመሪያውን የሪፎርም ስራ በተሳካ ሁኔ አካናውኗል፡፡
.
ሁለተኛውን የሪፎርም ምዕራፍ የተጀመረ ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወንና የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለመገንባት የሚያግዝ ‘‘The establishment of a project management unit at ACSO’’ ፕሮጀክት ቀርጾ አለም አቀፍ አማካሪ ድርጅቶችን በማወዳደር አሸናፊ ከሆነው CERFODES ከተባለ ድርጅት ጋር በመፈራረም ወደ ስራ ገብቷል፡፡
.
ፕሮጀክቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ሶስት ዓላማዎችን ያያዘ ሲሆን የመጀመሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን እና የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በማዘመን አንዲሁም የአዋጁን ተፈጻሚነት ለማሳለጥ ላይ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡