ድሬደዋ 8ተኛው የኢፌዴሪ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት የጋራ ጉባኤ ለማክበር እንግዶቿን ተቀብላለች፡:

ከጉባኤው ቀደም ብሎ የኤክስፐርቶች (NGO Desk heads) ሃላፊዎች ውይይት ዛሬ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የሁሉም ክልሎች በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትና ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ መክረዋል፡፡
የጉባኤው ዓላማ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቀሴ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ያላቸው የመንግስት አካላት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ በህግ አግብብ በመንቀሳቀስ የህዝብ ጥቅምን የሚያረጋግጥ ስራ እንዲያከናውን የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት፤የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቀሴና የተቋማትን አፈፃፀም በአገራዊ ደረጃ በመገምገም ክፍተቶችን በመለየት የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር ጋር በተያያዘ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ ነው፡፡