የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በተቋሙ የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች በክብር ተሸኝተዋል፡፡

በአመራር ብቃታቸው፣የአገልጋይነት ባህሪያቸው፣ሰው አክባሪነታቸውና ለዘርፉ ውጤት በማምጣት የሚታወቁት አቶ ጂማ ዲልቦ በመላው አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቦርድ አባላት ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ ሌላው አዲስ ወደ ተቋሙ ተሹመው የመጡትን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡