ባለስልጣን መስርያቤቱ ባዘጋጀው የማህበራዊ ተጠያቂነት መምርያ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገበት፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የማህበራዊ ተጠያቂነት መመርያን የማስተዋወቅና ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፍቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን የዚህ ውይይት ዓላማ መመርያውን ማስተዋወቅና ለመመርያው ግብዓት ለመሰብሰብ ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተው አዲስ በመመዝገብ ወደ ስራ ለሚገቡት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ስራ ላይ የሚያውሉት ይሆናል ብለዋል ፡፡ በውይይቱ ከገንዘብ ሚኒስትር ፣ከኦሮሚያ ፋይናንስ ቢሮ ተጠሪዎች እንዲሁም በአዲስ አበባና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በማህበራዊ ተጠያቂነት ላይ የሚሰሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡