የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ ግብርን አስጀመረ፡፡

የፍትህ ሚንስቴር ተጠሪ ተቋማት በጋራ በመሆን የችግኝ ተከላና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ ግብርን በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ዝዋይ ማዕከል በይፋ ተጀምሯል፡፡ በመርኃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚንስቴር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚንስትር ደዔታ አቶ አለምአንተ አግደውን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና እንግዶች የተገኙ ሲሆን በፌደራል ማረሚያ ቤቶች በሁሉም ማዕከላት ለምግብነት የሚውሉ ሁለት መቶ ሺህ ችግኞችን የመትከል መርኃ ግብርን “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል በይፋ አስጀምሯል፡፡
በእለቱ ከችግኝ ተከላ እስከ ምርት በሚል በማረሚያ ቤቱ የተሰሩ የግብርና ውጤቶች የተጎበኙ ሲሆን በማረሚያ ቤቱ የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችም ለምረቃ በቅተዋል፡፡ በተጨማሪም ዝዋይ በሚከኘው የተሃድሶና ማረሚያ ማዕከሉ ከ11 በላይ በሆኑ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከ280 በላይ ታራሚዎችን አስመርቋል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳመነ ዳሮታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በመርኃ ግብሩ ላይ ላደረገው አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን መሰል በሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ እየተገኘ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
Click the button