የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማህበራዊ ተጠያቂነት የትግበራ መምሪያ /Social Accountability mainstreaming guideline for CSOs/ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጎ ጸድቋል፡፡

በማኔጅመንት ደረጃ እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ በአዳማ ከተማ ውይይት በማድረግ ለሰነዱ ተጨማሪ ግብዓት በማሰባሰብ የማጽደቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በመድረኩ እንደገለጹት የዚህ ሰነድ አስፈላጊነት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የማህበራዊ ተጠያቂነትን በስራቸው አካተው መፈጸም የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ድርጅቶቹ አካቶ ትግበራ /mainstream/ አድርገው የማህበራዊ ተጠያቂነት መፈጸም ቢችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ውይይት የተደረገበት ይህ የትግበራ መምሪያ /guideline/ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እና አተገባበር ስልት እንዳለው በማንሳት ጽንሰ ሐሳቡ ግልጽ እንዲሆን በተቋም ደረጃ ሁሉም ሰራተኛ እና አመራሮች እንዲሁም በክልል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ውይይት አድርገውበታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ም/ዋና ዳይሬክተሩ የትግበራ መምሪያው ተፈጻሚ እንዲሆን እና ዘላቂነት እንዲኖረው አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሚና ይህ የትግበራ መምሪያ /guideline/ ከማዘጋጀት ጀምሮ እንዲፈጸም የመከታተልና የመደገፍ ሲሆን ይህንን ጋይድ ላይን ለማዘጋጀት መነሻ የሆነው ሀሳብ በአዋጅ 1113/2011 በፕሬአምፕል ላይ እንደተገለጸው የመንግስት አሰራር በግልጽነት፣በተጠያቂነትና በአሳታፊነት እንዲከናወን ለማድረግ የነቃና በነጻነት የተደራጀ ማኅበረሰብ መፍጠር የሚለው መሆኑ ከመድረክ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የተሰጡ አስተያየቶች ተካቶ ሰነዱ ጸድቋል፡፡
Click the button