ምቹ ሁኔታ ያለበት ተቋም መፍጠር እንፈልጋለን፡፡ ከዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ንግግር የተወሰደ።

ይህ የተባለው በተቋም ደረጃ የተዘጋጀ የጥቃት ጥበቃ መምሪያ ላይ ተከታታይ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡
ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው እንደገለጹት የመምሪያው ዓላማ የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና አጋሮች ከፍተኛ የሙያ ሥነ ምግባር ደረጃ እንዲኖራቸው፤ ይህንንም እንዲያጠናክሩና በጥቃት ጥበቃው መምሪያ እንዲመሩ ማገዝ እና ሁሉም የባለሥልጣኑ ሠራተኞችና አጋሮች የሚመሩበትን የጥቃት ጥበቃ ደረጃ በግልጽ በማስቀመጥ ማንኛውንም ሰው በባለሥልጣኑ ሠራተኞችና አጋሮች ሊደርስበት ከሚችል ፆታዊ/ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ብዝበዛና በደል መጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በዚህ መምሪያ መሠረት መሥሪያ ቤቱ አግባብነት ካላቸው የመንግሥት የሥራ ቅጥር አገልግሎት ሕጎች፣ መመሪያዎችና የአሠራር ሥርዓቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ተገቢ የሆኑ የጥቃት ጥበቃ አሠራሮችን ጥቅም ላይ ያውላል ብለዋል።
በመጨረሻም የዚህ መምሪያ መርህ ሰው መሆን እና የሰው ልጆች ክብር መሆኑን ገልጸው ተቋሙ ለስራ የተመቸ፣ ሁሉም ሰራተኛ፣ ባለጉዳይ፣ ጐብኚ ወዘተ በክብርና በስነስርዓት የሚያገለግልበትና የሚስተናገድበት ምቹ ሁኔታ ያለበት ተቋም መፍጠር እንፈልጋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ሰራተኞች አቶ መስፍን ማጎ እና አቶ ሱሌማን አብዱ ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡