ሶስተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ሲካሄድ የቆየው ሶስተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን በማጠቃለያ ፕሮግራሙ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ሃላፊዎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት አስፈላነትና በቀጣይ ድርጅቶቹ ተጠናክረው ስለሚሰሩበት ጉዳይ ተናግረዋል፡፡
በሶስት ቀናት ቆይታ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች በፓናል ውይይት የተዳሰሱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለበርካታ ጎብኚዎች ስራቸውን ማስተዋወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዓላማ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡