የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን ለማጎልበት በስነ ምግባር የታነፀ ባለሙያ ማፍራት አስፈላጊ ነው ተባለ::

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በስነምግባር ምንነት እና በስነምግባር እሴቶች ዙሪያ ለባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰጠ፡፡ በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ የብቃትና ሰው ሀብት ስራ አስፈጻሚ አቶ ደጀኔ ጌታቸው ለሰልጣኙ ባስተላለፉት መልዕክት የባለስልጣን መስሪቤቱ የሰራ አፈጻጸም ከአመት ወደ አመት እየሻሻለ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ1113/2011 በተሟላ መልኩ ለመተግበር ለሰራተኛው የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሁም የተቋሙን የውስጥ የመፈጸም እና የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስራዎች አሁን ላለው ውጤታማነት መሳያ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 17 መሰረት በእውነት፣ በታማኝነት ፣በስናምግባር ህዝብን አገለግላለሁ ብለን ቃል በገባነው መሰረት ህብረተሰባችንን ማገልገል አለብን ብለዋል፡፡ ሌላው ያነሱት መስሪያ ቤታችን በሁለተኛው የለውጥ ሂደት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ስኬታማ ስራዎችን በማጽናት ፣በማላቅ እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በመታገዝ የሚጠበቅብንን ውጤት ተግባራዊ ለማድረግ ስነ-ምግባር ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡
ከስልጠናዉ በኃላ የአሰራር ስራአቶቸን ተከትሎ ሙያዊ ስነ-ምግባርን በኃላፊነት በመወጣትና በማረጋገጥ የተቋሙን ተልዕኮና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል ብቁና ጥራት ያለው የሰው ሀብት እንዲኖር ማድረግ ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
ተቋማችን ሞዴል ተቋም እንዲሆን ለቴክኖሎጂ ትኩረት በመስጠት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ ስነ-ምግባር በየትኛውም ቦታ እንደ እለታዊ ልብሳችን ልንላበሰው የሚገባ መሆንንም አንስተዋል፡፡