``ተቋሙ ከሳሳካዋ አፍሪካ አሶስኤሽን / SASAKAWA AFRICA ASSOCIATION /ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡``

ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ካለው ጥሩ ስም እና ካከናወናቸው ተግባራት አንጻር የስምምነት ሰነዱን መፈራረማቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው በመግለጽ በተለይም ከመንግስት አካላት ጋር ያላቸው ቅንጅት፣የሃብት አጠቃቀምና አሳታፊነት ድርጅቱ አርዓያ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ድርጅቱ በግብርና ዘርፍ ቴክኖሎጂን ከማስተዋወቅ አንጻር ያከናወናቸውን ተግባራትን አጠናክሮ እንዲቀጥል በመግለጽ ሌሎች ድርጅቶችም ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ጉዳዬች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር ፈንታሁን መንግስቱ በበኩላቸው ድርጅቱ ግብርና ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ እና መሰረቱ ጃፓን ሃገር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በኢትጵያ 1986 ዓ.ም ጀምሮ ስራ የጀመረው ድርጅቱ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በየ5 ዓመቱ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ፤በየእርከኑ የሚገኙ የግብርና ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችን በመጠቀም፤ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን በማቅረብ፤ በተለያየ መንገድ ለገበሬዎች ድጋፍ የማድረግ ሰራ እንደሚሰራ በመግለጽ የዛሬው ስምምነትም በግብርና ዘርፍ የበለጠ ለመስራት እና ለመደገፍና ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር መሆኑን አንስተዋል፡፡