የሲቪል ማህበ ረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ጋር በመተባበር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ላሉት የፋይናንስ ተቋማት ሃላፊዎችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሃላፊዎች በአዳማ ከተማ አዋጅ 1113/2011እና አዋጁን ተከትሎ በወጣው 6 መመርያዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተረፈ ደጌቲ እንደተናገሩት ይህ ስልጠና የፋይናንስ ተቋማት እና ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጋራ በአዋጁና በመመርያዎቹ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ ፋይዳው የጎላ መሆኑን በመናገር ሁለቱም በጋራ ለማህበረሰቡ እንደመስራታቸው ያላቸውን ጥያቄዎች በጋራ ለመመለስ እና በአዋጁና መመርያው ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሱሲ ፍርደሳ በበኩላቸው ይህ ዛሬ የምንወስደው ስልጠና አዋጁንና መመርያዎችን በተገቢው መንገድ ተረድተን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለመደገፍ፣ ክትትል ለማድረግ እና በማህበረሰቡ ስም የሚመጣውንም ሃብት በተገቢው አገልግሎት ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ዕድል ይፈጥርልናል ብለዋል ፡፡
አክለውም በስልጠናው የተሳተፋችሁ የስራ ሃላፊዎችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደተቋማችሁ ስትመለሱ በስራችሁ ላሉት ባለሞያዎች አዋጁንና መመርያዎቹን በተገቢው በማስገንዘብ የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት ይኖርባችዋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
አቶ ተሾመ ወርቁ እና አቶ ዳንኤል ግዛው በአዋጅ 1113/2011ን ጨምሮ በአስተዳደራዊ ወጪን አፈፃፀም መመርያ ቁጥር 847/2014፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለማስተዳደር የወጣን መመርያ ቁጥር 848/2014፣ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሂሳብ አጣሪዎችና ስለንብረት ግዢ ፣ሽያጭ ና አወጋገድ የወጣ መመርያ ቁጥር 850/2014፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ሚሰማሩበት ሁኔታ የወጣ መመርያ ቁጥር 937/2015፣ጥቅም ግጭትን ለማስቀረት የወጣ መመርያ ቁጥር 939/2015 እና ስለድርጅቶች መዋሃድ ፣መከፋፈልና መለወጥ የወጣ መመርያ ቁጥር 936/2014 ላይ መመርያዎቹ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡