የጃፓን፣ ኮሪያ ኢትዮጵያ ወዳጅነት ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር የአስር ሺህ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግም ተጠቁሟል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ለፋውንዴሽኑ ሰብሳቢ ዮንግዎ ሊ (Yongwoo lee) ድርጅቱ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ ስለሚቀሳቀስበት ሁኔታ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ ፋውንዴሽኑ ለሚያደርገው ድጋፍም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ትልቅ ክብር እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የድርጅቱ ሰብሳቢ የሆኑት ዮንግዎ ሊ (Yongwoo lee) የኢትዮ ኮሪያ ዘማቾች በኮሪያ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ሄደው ብዙ ተጋድለዋል ያሉ ሲሆን ይህ ስራቸው የሚዘነጋ እንዳልሆነ አንስተዋል፡፡ የኢትዮ ኮሪያ ዘማቾች ከኪሳቸው እያወጡ ወላጅ አልባና ለችግር የተጋለጡ ህጻናትን እየረዱ እንደሚገኙ በመጠቆም ይህን የድርጅቱን እንቅስቃሴ ለመደገፍና ለማበረታታት የአስር ሺህ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርጉ አክለው ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በተደረገለት ጥሪ መሰረት በኢትዮጵያ ቢሮውን ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ሃላፊው በነገው እለት በኢትዮ ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ለማስቀመጥ እና ለማህበሩ ድጋፍ ለማድረግ መርኃ ግብር መዘጋጀቱን ጠቁመዋል ፡፡