ኤስኤን ቪ የተባለ ድርጅት በባለስልጣን መስሪቤቱ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ከተቋቋመ ረጅም አመታት ያስቆጠረ ሲሆን በኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ ድርጅት በዋናነት በአርባምንጭ ዙሪያ ጋንታ ካፍማ ቀበሌ የአርሷደሩን የግብርና ስራዎች በዘመናዊ መልክና በቴክኖሎጂ በማገዝ እና በሙዝ ምርታማነት ላይ ጥሩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ኤስኤን ቪ ድርጅት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ማናጀር ወ/ሪት አለምጸአይ ገነት ገልጸዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኋላ የልማት አጋር መሆናቸውን መንግስ በፖሊሲ ደረጃ መያዙን አውስተው ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ መንግስት ብቻውን የአገርን ልማት መስራት ስለማይችል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከዚህ ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዳዲስ እሳቤዎችን ፣እውቀቶችን እና ቴክኖሎጂዎን ለአርሷአደሩ የሚያስተዋውቁ ከሆነ መለወጥ የማይፈልግ ማህበረሰብ እንደሌለ ገልጸው በነበረን እውቀት ላይ ተጨምሮ ለአገር ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ ሌላው ያነሱት በክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት በቅርቡ መጀመሩ የሚታወቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እሳቤው የአርሷደሩ ሌማት ሙሉ ይሁን ስንል ሁላችንም ተግተን ስንሰራ ሌማታችን ሙሉ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኤስ ኤን ቪ ድርጅት ከአርሷአደሩ ጋር እየሰሩት ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚበረታታ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ሌሎችም ድርጅቶች ልምድ በመውሰድ እና በመተጋገዝ ትልቅ ስራ መስራት እንደሚቻል አንስተዋል፡፡