አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከተሻሻሉ ህጎች ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 አንዱ ነው፡፡ አዋጅ 1113/2011 በተሟላ መልኩ ለማስፈጸም በባለስጣን መስሪያ ቤቱ አስራ ሰባት መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ከተዘጋጁት መመሪያዎች ውስጥ ስምንት መመሪያዎች በቦርዱ ፀድቀው ወደስራ አስገብቷል፡፡ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስደተዳደሮች ለሚገኙ ለፋይናንስ ቢሮ ዴስክ ባለሙዎችና ለተፈራራሚ አካላት በጸደቁ መመሪያዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ለመስጠት እቅድ የተያዘ ሲሆን አስካሁን በአርባምንጭ፣በድሬደዋ እና በቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመመሪያዎቹ ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል:: ከፀደቁት መመሪያዎች ውስጥ የጥቅም ግጭት ለማስቀረት የወጣ መመሪያ ቁጥር 936/2015፣ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ የሚሰማሩበት ሁኔታ የወጣ መመሪያ ቁጥር 936/2015 እና የአገር በቀል ድርጅቶች ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 938/2015 እንዲሁም ስለድርጅቶች መዋሀድ፣መከፋፈል፣መለወጥና መፍረስ የወጣ መመሪያ ቁጥር936/2015 ናቸው፡፡ እነዚህን መመሪያዎች ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለፋይናንስ ቢሮ ዴስክ ባለሙዎች ለተፈራራሚ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች አዘጋጅቶ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግስት ለፋይናንስ ቢሮ ዴስክ ባለሙዎች በአርባምንጭ ከተማ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይረፌክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት በአገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የዜጎች የመደራጀት መብት ሙሉበሙሉ ያከበረ፣ዴሞክራሲያዊ ባህል ያጎለበተ እንዲሁም የነቃና የተደራጀ ማህበረሰብን ለመፍጠር ወሳኝ የሆነና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአገር ልማት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም አዋጁ ከፀደቀ ቀን አንስቶ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ2200 በላይ አዳዲስ ድርጅቶች ተመዘገበው ወደስራ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለአገራችን ሁለንተናዊ እድገትና ልማት፣ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት፣ በአገረ መንግስት ግንባታና ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ አዎንታዊ ሚና እንዳላቸው በመጥቀስ ዘርፉ እንዲጠናከርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከመንግስት ጋር የነበራቸውን አሉታዊ ግንኙነት ወደ አዎንታዊ በመለወጥ የልማት አጋርነት መሰረት በማድረግ መልካም አስተዳደር ችግሮች፣ግልፀኝነትን፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የተደራጀ የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች መኖር አስፈላጊ መሆኑን ዋና ዳይሬክሩ አንስተዋል፡፡ ሌላው ያነሱት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት የለውጥ ስራዎች መሰራታቸውን፣ የምዝገባና የክትትል ስራዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ኢ-ሰርቪስ አግልግሎት መቀየራቸውን እንዲሁም ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር ጉባኤ ተመስርቶ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህን መመሪያዎች በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስደተዳደሮች ለሚገኙ ለፋይናንስ ቢሮ ዴስክ ባለሙዎችና ለተፈራራሚ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ለማዘጋጀት ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም አመስግነዋል፡፡ ቀድመው በጸደቁ አራት መመሪያዎች ላይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ይታወቃል::